La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በተሰጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት፣ ዐሥር የወርቅ መቅረዞች ሠርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን በስተሰሜን አኖራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሥሩንም መቅረዞች እንደ ሥርዓታቸው ከወርቅ ሠርቶ አምስቱን በቀኝ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰሎሞን በተዘጋጀው ዕቅድ መሠረት ዐሥር መቅረዞችን ከወርቅ አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዐሥሩንም መቅረዞች እንደ ሥርዓታቸው ከወርቅ ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 4:7
13 Referencias Cruzadas  

አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።


በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት አም​ስቱ በቀኝ፥ አም​ስ​ቱም በግራ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከጥሩ ወርቅ የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም መቅ​ረ​ዞች፥ የወ​ር​ቁ​ንም አበ​ባ​ዎ​ችና ቀን​ዲ​ሎች፥ መኮ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም፥


ደግ​ሞም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባ​ዮ​ችና በዙ​ሪ​ያው ለሚ​ሆኑ ጓዳ​ዎች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ ለን​ዋየ ቅድ​ሳ​ቱም ለሚ​ሆኑ ዕቃ ቤቶች፥ ለቀ​ሩ​ትም በመ​ን​ፈሱ ላሰ​በው ሁሉ ምሳ​ሌን ሰጠው።


ለወ​ርቁ ዕቃ ወር​ቁን በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚ​ዛን ሰጠው፤


ለወ​ር​ቁም መቅ​ረ​ዞ​ችና ለቀ​ን​ዲ​ሎ​ችም ወር​ቁን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም መቅ​ረ​ዞች እንደ መቅ​ረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤


ዕው​ቀት እንደ ተሰ​ጠው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።