Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሰሎሞን በተዘጋጀው ዕቅድ መሠረት ዐሥር መቅረዞችን ከወርቅ አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በተሰጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት፣ ዐሥር የወርቅ መቅረዞች ሠርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን በስተሰሜን አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አሥሩንም መቅረዞች እንደ ሥርዓታቸው ከወርቅ ሠርቶ አምስቱን በቀኝ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዐሥሩንም መቅረዞች እንደ ሥርዓታቸው ከወርቅ ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 4:7
13 Referencias Cruzadas  

በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፥ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፥ አበባዎች፥ የመብራት ቀንዲሎች፥ የእሳት መቈስቈሻዎች፥


እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው።


ለአደባባዮቹና በዙሪያቸው ላሉት ክፍሎች፥ ለቤተ መቅደሱ ዕቃና ለእግዚአብሔር ለሚቀርቡ መባዎች የዕቃ ግምጃ ቤት በሐሳቡ የነበረውን ሁሉ የአሠራር ዕቅድ ጨምሮ ሰጠው።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ኮከቦችና የሰባቱም የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ኮከቦች የሰባቱ አብያተ ክርስቲያን መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞችም ሰባት አብያተ ክርስቲያን ናቸው።”


እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው።


ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት “ይህ ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ በሥራ ላይ እንዳውለው በሰጠኝ መመሪያ መሠረት በጽሑፍ የሰጠኝ ዕቅድ ነው” አለ።


ለያንዳንዱ መቅረዝና መብራት የሚሆን ወርቅ፥ እንዲሁም ለመቅረዙና ለመብራቱ የሚሆን ብር መዝኖ ሰጠው።


ሑራምም አምስቱን የዕቃ ማስቀመጫዎች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ፥ የቀሩትንም አምስቱን በቤተ መቅደሱ በስተ ሰሜን በኩል አቆመ፤ ገንዳውን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ምሥራቅ ማእዘን ላይ አቆመው።


ለተለያዩ የአገልግሎት ዐይነቶች መጠቀሚያ የሚሆኑትን ዕቃዎች መሥሪያ እንዲሆኑ የብሩንና የወርቁን መጠን በሚዛን ወሰነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios