La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ውፍ​ረ​ት​ዋም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከን​ፈ​ሯም እንደ ጽዋ ከን​ፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠ​ርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም ማድጋ ትይዝ ነበር ሠር​ቶም ፈጸ​ማት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ያህል ውሃ የሚይዝ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሁሉም ጀርባቸው ወደ ውስጥ ነበር። የገንዳው ጐኖች ውፍረት ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ሲሆን፥ ክፈፉም እንደ ኩባያ ክፈፍ ሆኖ እንደ አሸንድዬ አበባ ወደ ውጪ የተቀለበሰ ነው፤ በርሜሉ ሥልሳ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም አንድ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 4:5
4 Referencias Cruzadas  

ኩሬ​ውም በዐ​ሥራ ሁለት በሬ​ዎች ምስል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስ​ቱም ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ኩሬ​ውም በላ​ያ​ቸው ነበረ፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።


ውፍ​ረ​ቱም አንድ ጋት ነበረ። ከን​ፈ​ሩም እንደ ጽዋ ከን​ፈር ተሠ​ርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበ​ባ​ዎች ሆኖ ተከ​ር​ክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይይዝ ነበር።


ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን ሠሩ​ላ​ቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተ​ሠ​ራች ኵሬም በላ​ያ​ቸው ነበ​ረች፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።


በዙ​ሪ​ያ​ውም አንድ ጋት የሚ​ያ​ህል ክፈፍ አድ​ር​ግ​ለት፤ የወ​ር​ቅም አክ​ሊል በክ​ፈፉ ዙሪያ አድ​ር​ግ​ለት።