2 ዜና መዋዕል 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ ዐሥር፥ እንደ በሬዎች ያሉ ቅርጾች በኩረው ላይ አዞረበት፤ ኩሬውንም በቀለጠ ጊዜ የበሬዎቹም ቅርጾች በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገንዳው የውጪው ክፈፍ ዙሪያው በሙሉ አንዱ በሌላው ላይ የተነባበረ ሆኖ በሁለት ረድፍ የተሠሩ ጌጦች ነበሩት፤ እነዚህም ጌጦች በሙሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በበሬዎች ቅርጽ የተሠሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ አሥር፥ ጕብጕቦች አዞረበት፤ ኵሬውም በቀለጠ ጊዜ ጕብጕቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። |
ዐሥራ ሁለት በሬዎችን ሠሩላቸው። ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተሠራች ኵሬም በላያቸው ነበረች፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ።
የፊታቸው አምሳያ እንደዚህ ነው፦ ለአራቱ ሁሉ በቀኛቸው የሰው ፊትና የአንበሳ ፊት አላቸው፤ ለአራቱም ሁሉ በግራቸው የእንስሳ ፊትና የንስር ፊት አላቸው።
ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፤ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።
አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።
ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።