La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ወ​ጣ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ያለ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት አሳድዶ ያስወጣቸውን የአሕዛብን አስጸያፊ ልማድ በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት በጌታ ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል፥ ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኵሰት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 33:2
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው አሕ​ዛብ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት፥ በኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንና ሐው​ል​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤


የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ራ​ቃ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


ነገር ግን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠሩ ዘንድ ምናሴ አሳ​ታ​ቸው።


ደግ​ሞም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለም​ስሉ ሠዋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛ​ብም ክፉ ልማድ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


አሁ​ንም ቸር​ነ​ት​ህን እየ​ለ​መ​ንሁ በልቤ ጕል​በት እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።


የይ​ሁ​ዳም ታላ​ላቅ ሰዎች ካህ​ና​ቱና የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ በአ​ሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ሁሉ መተ​ላ​ለ​ፍን አበዙ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አረ​ከሱ።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በት​እ​ዛዜ አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩት እንደ አሕ​ዛብ ሕግ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።”


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ ባጠፋ ጊዜ፥ አን​ተም በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥ ከፊ​ትህ ከጠፉ በኋላ እነ​ር​ሱን ለመ​ከ​ተል እን​ዳ​ትሻ፥


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።


አንተ የም​ት​ወ​ር​ሳ​ቸው እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሞራ ገላ​ጮ​ች​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ያዳ​ም​ጣሉ፤ ለአ​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ምና።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ እነ​ዚያ አሕ​ዛብ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ታደ​ርግ ዘንድ አት​ማር።