La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ራም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮሣፍጥ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ኢዮራምም በምትኩ ነገሠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮሣፍጥም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮሣፍጥ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮሣፍጥም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 21:1
8 Referencias Cruzadas  

አሣ​ሄ​ል​ንም አን​ሥ​ተው በቤተ ልሔም በአ​ባቱ መቃ​ብር ቀበ​ሩት፤ ኢዮ​አ​ብና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በሩ ሰዎ​ቹም ሌሊ​ቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬ​ብ​ሮ​ንም አነጉ።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም አብያ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የማ​ር​ሶስ ሰው የኢ​ያ​ድያ ልጅ አል​ዓ​ዛር፥ “ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​ብ​ረ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን አፍ​ር​ሶ​ታል” ብሎ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገረ። መር​ከ​ቦ​ቹም ተሰ​በሩ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም ይሄዱ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያ​ዝ​ን​ለት ሄደ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ እንጂ በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ሰሎ​ሞ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ሮብ​ዓም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።