2 ዜና መዋዕል 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ አፍ የሐሰት መንፈስን አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በአንተ ላይ ክፉ ተናግሮብሃል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ እነሆ፣ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ የሐሰት መንፈስ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንደሚያመጣብህ ተናግሯል”። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ ጌታ በእነዚህ በነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስን አኑሮአል፤ ጌታም በአንተ ላይ ክፉ ተናግሮብሃል።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚክያስም “እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ በእነዚህ በነቢያትህ አንደበት የሐሰት መንፈስ እንዳስቀመጠ ታያለህን? ይህንንም ያደረገው በአንተ ላይ ጥፋትን ስለ ወሰነብህ ነው!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስን አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በአንተ ላይ ክፉ ተናግሮብሃል።” |
እርሱም፥ “ወጥቼ በነቢያት ሁሉ አፍ የሐሰት መንፈስ እሆናለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “ታታልለዋለህ፤ ይቀናሃል፥ ውጣ፤ እንዲህም አድርግ” አለው።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ክፉ እንጂ ከቶ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለው። ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሡ እንዲህ አይበል” አለው።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ሲል ላከ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው” ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም ዱር አውሬዎች መጥተው ኵርንችቱን ረገጡት።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራቴን ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
እግዚአብሔር የሚያስት መንፈስን ልኮባቸዋልና፤ ሰካርም፥ ደም ያዞረውም እንዲስት እንዲሁ ግብፃውያን በሥራቸው ሁሉ ሳቱ።
አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፤ ምክርንም እመክርባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።”
ነቢዩም ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።