በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
2 ዜና መዋዕል 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ብሩንና ወርቁን፥ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባንም እንጨት በብዛት በቆላ እንደሚገኝ ሾላ በይሁዳ አኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ በኢየሩሳሌም ብሩንና ወርቁን እንደ ማንኛውም ድንጋይ፣ የዝግባውንም ዕንጨት ብዛት በየኰረብታው ግርጌ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቈላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ወርቅና ብር ከመብዛቱ የተነሣ እንደ ድንጋይ ተራ ነገር ነበር፤ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ዛፍ ይቈጠር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቈላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ። |
በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥሃለሁ። ካንተ በፊት ለነበሩ ነገሥታት ያልተሰጠውን፥ ከአንተም በኋላ ለሚነሡ የማይሰጠውን ብልፅግናን፥ ገንዘብንና ክብርን እሰጥሃለሁ።”
ንጉሡም ወርቁንና ብሩን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባውንም እንጨት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ብዛት አደረገው።
በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን እሰጥሻለሁ። ለአለቆችሽም ሰላምን፥ ለመኳንንትሽም ፍርድን አደርጋለሁ፤