1 ጢሞቴዎስ 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብ ክስ አትቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ካልመሰከሩበት በቀር በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ላይ የሚቀርበውን ክስ አትቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። |
እኔም፦ ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ሳይቆም፥ ለተከሰሰበትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያገኝ ማንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሕግ አይደለም ብየ መለስሁላቸው።
“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለሚሠራት ኀጢአት ሁሉ በማንም ላይ አንድ ምስክር አይሁን፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸናል።