መጻሕፍትን መርምሩ፤ በእነርሱ የዘለዓለም ሕይወትን የምታገኙ ይመስላችኋልና፤ እነርሱም የእኔ ምስክሮች ናቸው።
1 ጢሞቴዎስ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝቡ በማንበብ፥ በመምከርና በማስተማር ትጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ በማንበብ፥ በመስበክና በማስተማር ትጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ። |
መጻሕፍትን መርምሩ፤ በእነርሱ የዘለዓለም ሕይወትን የምታገኙ ይመስላችኋልና፤ እነርሱም የእኔ ምስክሮች ናቸው።
በተሰሎንቄ ካሉትም እነርሱ ይሻላሉ፤ በፍጹም ደስታ ቃላቸውን ተቀብለዋልና፤ ነገሩም እንደ አስተማሩአቸው እንደ ሆነ ለመረዳት ዘወትር መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።
የሚመክርም በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥም በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛም በትጋት ይግዛ፤ የሚመጸውትም በደስታ ይመጽውት።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሁላችሁ በምትሰበሰቡበት ጊዜ መዝሙር አላችሁ፤ ትምህርት አላችሁ፤ መግለጥ አላችሁ፤ በቋንቋ መናገር አላችሁ፤ መተርጐምም አላችሁ፤ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት።
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቋንቋ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው?
መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው። አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህችንም ሥርዐት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንብበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል፤ አስተዋይም ትሆናለህ።