ወሬውን ያመጣለት ጎልማሳም አለ፥ “በጌላቡሄ ተራራ ተዋግተው ወደቁ፤ እነሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረገሎችና ፈረሰኞችም ተከትለው ደረሱበት።
1 ሳሙኤል 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ቤትሳሚስ አቅጣጫ ወደ ገዛ አገሩ የሚሄድ ከሆነ፣ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፣ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልከቱም፥ በድንበሩም መንገድ ወደ ቤትሳሚስ ቢወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እግዚአብሔር ነው፥ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን። |
ወሬውን ያመጣለት ጎልማሳም አለ፥ “በጌላቡሄ ተራራ ተዋግተው ወደቁ፤ እነሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረገሎችና ፈረሰኞችም ተከትለው ደረሱበት።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤትሳሚስ ላይ እርስ በርሳቸው ተያዩ።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ።
ፍልስጥኤማውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰረገላውም ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፤
ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው “እምቧ” እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆችም እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።
እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳኑን ታቦት ብትሰድዱአት ስለ አሳዘናችሁአት የበደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶዋን አትስደዱአት፤ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፤ ስርየትም ይደረግላችኋል፤ አለዚያ ግን የእግዚአብሔር እጅ ከእናንተ አይርቅም” አሉ።