Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን ይዘው እምቧ እምቧ እያሉ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሳሚስ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዦችም እስከ ቤትሳሚስ ድንበር ተከተሏቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው እምቧ እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፥ የፍልስጥኤማውያንም አለቆች እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላቸው ይሄዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 6:12
7 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “በተ​ራ​ራው በኩል እና​ል​ፋ​ለን፤ እኛም ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም ከው​ኃህ ብን​ጠጣ ዋጋ​ውን እን​ከ​ፍ​ላ​ለን፤ ይህ ምንም አይ​ደ​ለም፤ በተ​ራ​ራው እን​ለፍ” አሉት።


ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የወ​ርቁ አይ​ጦ​ችና የአ​ካ​ላ​ቸው እባ​ጮች ምሳሌ ያሉ​በ​ት​ንም ሣጥን በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ጫኑ።


የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎ​ችም በእ​ርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ተቀ​በ​ሉ​አት።


ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል።


በማ​ኪ​ስና በሰ​አ​ል​ቢን፥ በቤት ሳሚ​ስና በኤ​ሎ​ን​ቤ​ት​ሐ​ናን የዴ​ቀር ልጅ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios