1 ሳሙኤል 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? እነዚህ አማልክት ግብፃውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? ግብጻውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ እነዚሁ አማልክት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ እነዚሁ አማልክት ናቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? እነርሱ ግብጻውያንን በበረሓ በተለያዩ መቅሠፍቶች የመቱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዮልን፥ ከእነዚህ ከኃያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? እነዚህ አማልክት ግብጻውያንን በምድረ በዳ በልዩ በልዩ መቅሠፍት የመቱ ናቸው። |
ግብፃውያንም እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው በአወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ በሰውነትህ፥ በአገልጋዮችህም፥ በሕዝብህም ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እልካለሁ።
እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውሕሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።
ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው፥ “አማልክት ወደ እነርሱ ወደ ሰፈር መጥተዋል” አሉ። ደግሞም እንዲህ አሉ፥ “ወዮልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድነን፤ ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር አልሆነምና።
እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እናንተ ባሪያዎች እንዳደረጋችኋቸው ዕብራውያን ባሪያዎች እንዳያደርጓችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።”
የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አትቀመጥ” አሉ።