ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
1 ሳሙኤል 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምራቱም የፊንሐስ ሚስት አርግዛ ልትወልድ ተቃርባ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ታቦት እንደ ተማረከች፥ አማቷና ባልዋም እንደ ሞቱ በሰማች ጊዜ አለቀሰች፤ ከዚያም በኋላ ወለደች። ሕማምዋም ተመለሰባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፣ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፣ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፥ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፥ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፥ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፊንሐስ ሚስት የነበረችው የዔሊ ምራት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት መማረኩን፤ ዐማትዋና ባልዋ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ በድንገተኛ ምጥ ተይዛ ወለደች፤ ምጡም ጸንቶባት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምራቱም የፊንሐስ ሚስት አርግዛ ልትወልድ ተቃርባ ነበር፥ የእግዚአብሔርም ታቦት እንደ ተማረከች፥ አማትዋና ባልዋም እንደ ሞቱ በሰማች ጊዜ ምጥ ደርሶባት ነበርና ተንበርክካ ወለደች። |
ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
የእግዚአብሔርንም ታቦት ባሰባት ጊዜ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ፥ ደንግዞም ነበርና ጀርባው ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።
ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ” አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፤ ልብዋም አያስታውስም ነበር።