እንዲህም ሆነ፦ ይስሐቅ ፈጽሞ ከአረጀ በኋላ ዐይኖቹ ፈዝዘው አያይም ነበር። ታላቁን ልጁን ዔሳውንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
1 ሳሙኤል 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፤ ዐይኖቹም ፈዝዘው አያይም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ስለ ነበር ዐይኖቹ ደክመው ማየት ተስኗቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ስለ ነበር ዐይኖቹ ደክመው ማየት ተስኗቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዘመን ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዐይኑም ፈዞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ ዓይኖቹም ማየት እስኪሳናቸው ድረስ ፈዝዘው ነበር። |
እንዲህም ሆነ፦ ይስሐቅ ፈጽሞ ከአረጀ በኋላ ዐይኖቹ ፈዝዘው አያይም ነበር። ታላቁን ልጁን ዔሳውንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
የኢዮርብዓምም ሚስት እንዲሁ አደረገች፤ ተነሥታም እንጀራ፥ የወይን ዘለላና አንድ ማሠሮ ማር በመያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸምገሉ ዐይኖቹ ፈዝዘው ነበርና ማየት አልቻለም።