La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን ሳኦል ሦስ​ቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በአ​ንድ ላይ ሞቱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልና ሦስት ልጆቹ፣ ዐብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በአንድ ላይ በዚያ ቀን ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ፥ አብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በዚያኑ ቀን ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ ሳኦልና ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ እንዲሁም ጋሻጃግሬው የሞቱት በዚህ ዐይነት ሲሆን፥ የሳኦልም ተከታዮች በዚያን ቀን አብረዋቸው ሞቱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን ሳኦል ሦስቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግሬውም ሰዎቹም ሁሉ በአንድ ላይ ሞቱ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 31:6
14 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከመ​ግ​ደል ተመ​ለሰ፤ ዳዊ​ትም በሴ​ቄ​ላቅ ሁለት ቀን ተቀ​መጠ።


በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።


ሳኦ​ልና ሦስ​ቱም ልጆቹ የቤ​ቱም ሰዎች ሁሉ በዚ​ያች ቀን በአ​ንድ ላይ ሞቱ።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ጌል​ገላ ሄዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ቀብቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ አነ​ገ​ሠው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህል ቍር​ባ​ንና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደ​ረጉ።


የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።”


ነገር ግን ክፉ ብት​ሠሩ እና​ን​ተም፥ ንጉ​ሣ​ች​ሁም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


ደግ​ሞም ዳዊት አለው፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ገ​ደ​ለው፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ካል​ሞተ፥ ወይም ወደ ጦር​ነት ወርዶ ካል​ሞተ እኔ አል​ገ​ድ​ለ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከአ​ንተ ጋር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ ነገም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉ ልጆ​ችህ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍራ ደግሞ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰ​ይፉ ላይ ወደቀ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሞተ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።