1 ሳሙኤል 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤ ከነገረህና ከሰማኸው ነገር ሁሉ የሸሸግኸኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፤ እንዲህም ይጨምርብህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊም፣ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊም፥ “እርሱ የነገረህ ነገር ምንድነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ የከፋም ያምጣብህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሊም “እግዚአብሔር የነገረህ ቃል ምንድን ነው? ከእኔ ምንም ነገር አትደብቅ፤ አንዳች ነገር ብትደብቅ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ብርቱ ቅጣት ያምጣብህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድር ነው? ከእኔ አትሸሽግ፥ ከነገረህ ነገር ሁሉ የሸሸግኽኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፥ እንዲህም ይጨምርብህ አለው። |
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ” ብሎ ማለ።
እግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ማለለት እንዲሁ ከእርሱ ጋር ዛሬ ባላደርግ እግዚአብሔር በአበኔር ይህን ያድርግበት፤ ይህንም ይጨምርበት።
ንጉሡም፥ “የሣፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በላዩ ያደረ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርገኝ እንዲህም ይግደለኝ” አለ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፥ “አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።
ነቢዩ ኤርምያስም አላቸው፥ “ሰምታችኋል፤ እነሆ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም የሚመልስልኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ ከእናንተም አንድም ቃል አልሸሽግም።”
የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?
ወደ እርሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም በለዓምን አለው፥ “እግዚአብሔር ምን አለ?”
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።
በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።
አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።
ለናባልም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ብንተው፥ እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ፤ እንዲህም ይጨምር” ብሎ ነበር።