አባቱም፥ “ከቶ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ አልከለከለውም ነበር፤ እርሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እርሱንም ከአቤሴሎም በኋላ ወልዶት ነበር።
1 ሳሙኤል 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹ በእኔ ላይ የንቀት ተግባር ሲፈጽሙ እርሱ ስላልገሠጻቸው ቤተሰቡን ለዘለዓለም እቀጣለሁ ብዬ ነግሬዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ የእርግማን ነገር እንዳደረጉ አውቆ አልከለከላቸውምና ስለ ኃጢአቱ በቤቱ ለዘላለም እንድፈርድ አስታውቄዋለሁ። |
አባቱም፥ “ከቶ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ አልከለከለውም ነበር፤ እርሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እርሱንም ከአቤሴሎም በኋላ ወልዶት ነበር።
ንጉሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአባቴ በዳዊት ላይ የሠራኸውን፥ ልብህም ያሰበውን ክፋት ሁሉ ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም ክፋትህን በራስህ ላይ ይመልሳል።
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
አሁንም ፍጻሜ በአንቺ ላይ ደርሶአል። ቍጣዬንም እሰድድብሻለሁ፤ እንደ መንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፤ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም በዚያ ወራት ያለውን ፈራጁን ባይሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእስራኤልም ዘንድ ክፉውን አስወግዱ፤