Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አባ​ቱም፥ “ከቶ ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” ብሎ አል​ከ​ለ​ከ​ለ​ውም ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እር​ሱ​ንም ከአ​ቤ​ሴ​ሎም በኋላ ወል​ዶት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አባቱም፣ “ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?” ብሎ ገሥጾት አያውቅም ነበር፤ አዶንያስም እጅግ መልከ መልካምና የአቤሴሎም ታናሽ ወንድም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አባቱም በሕይወቱ ሳለ፦ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ ከቶ ተቆጥቶት አያውቅም ነበር። ደግሞም መልከ መልካም ነበር፤ የተወለደውም ከአቤሴሎም በኋላ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አባቱም ከቶ በሕይወቱ ሳለ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ አልተቆጣውም ነበር፤ እርሱ ደግሞ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ ከአቤሴሎምም በኋላ ተወልዶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:6
11 Referencias Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ እንደ አቤ​ሴ​ሎም በው​በቱ ያማረ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ግሩ እስከ ራሱ ድረስ ነውር አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ለእ​ናቱ መልሶ፥ “ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ለአ​ዶ​ን​ያስ ለምን ትለ​ም​ኚ​ለ​ታ​ለሽ? ታላቅ ወን​ድሜ ነውና መን​ግ​ሥ​ትን ደግሞ ለም​ኚ​ለት፤ ካህ​ኑም አብ​ያ​ታ​ርና የሶ​ር​ህያ ልጅ የጭ​ፍ​ሮች አለቃ ኢዮ​አብ ደግሞ ከእ​ርሱ ጋር ናቸው” አላት።


ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥


አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና።


እር​ሱም ሮጦ ከዚያ አመ​ጣው፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ መካ​ከል አቆ​መው፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ረዥም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ከት​ከ​ሻው በታች ሆኑ።


ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ።


ለእ​ር​ሱም ሳኦል የሚ​ባል የተ​መ​ረጠ መል​ካም ልጅ ነበ​ረው፤ በም​ድር ሁሉ ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ርሱ ይልቅ መል​ካም የሆነ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ከት​ከ​ሻ​ውና ከዚ​ያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos