La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! ጌታ በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ግን አቢሳን፦ “ልትገድለው አይገባህም! ቀብቶ ያነገሠውን ንጉሥ የሚጐዱ ሰዎችን እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም አቢሳን፦ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን የሚዘረጋ ንጹሕ አይሆንምና አትግደለው አለው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 26:9
11 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም፥ “ትገ​ድ​ለው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጅ​ህን ስት​ዘ​ረጋ እን​ዴት አል​ፈ​ራ​ህም?” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! ዛሬ ታስ​ቱኝ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገ​ሥሁ አላ​ው​ቅ​ምን?”


የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።


የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዐ​መፅ ፈሳ​ሽም አወ​ከኝ፤


በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤


ክፉ ላደ​ረ​ጉ​ብ​ኝም ክፉን መል​ሼ​ላ​ቸው ብሆን፥ ጠላ​ቶቼ ዕራ​ቁ​ቴን ይጣ​ሉኝ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


አቢ​ሳም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ አሁ​ንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከም​ድር ጋር ላጣ​ብ​ቀው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ደ​ግ​መ​ውም” አለው።