1 ሳሙኤል 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! ነገር ግን በራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውሃ መያዣውን ያዝና እንሂድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በቀባው ላይ እጄን ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ! ነገር ግን በራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውሃ መያዣውን ያዝና እንሂድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው ንጉሥ ላይ ጒዳት የማድረስ ተግባርስ ከእኔ ይራቅ! ይልቅስ ጦሩንና ውሃ መቅጃውን ይዘንበት እንሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፥ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ አለ። |
ዳዊትም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! ዛሬ ታስቱኝ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእስራኤል የሚሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእስራኤል ላይ እንደ ነገሥሁ አላውቅምን?”
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”
እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ።
በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች ወጣ፤ በዚያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ወደዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።