እርሱም አለው፥ “ስለ እርስዋ የነገርኸኝን ያችን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ፥ እንዳልኸው ልመናህን ተቀብዬሃለሁ፤
1 ሳሙኤል 25:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፥ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃልሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊትሽንም እንዳከበርሁ ተመልከቺ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀብሎ፣ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፤ ቃልሽን ሰምቻለሁ፤ የጠየቅሽኝንም ተቀብያአለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀብሎ፥ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፤ ቃልሽን ሰምቻለሁ፤ የጠየቅሽኝንም ተቀብያአለሁ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ዳዊት ያመጣችለትን ስጦታ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ተመልሰሽ ሂጂ፤ ልመናሽን ሰምቼአለሁ፤ የጠየቅሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፦ በደኅና ወደ ቤትሽ ሂጂ፥ እነሆ፥ ቃልሽን ሰማሁ፥ ፊትሽንም አከበርሁ አላት። |
እርሱም አለው፥ “ስለ እርስዋ የነገርኸኝን ያችን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ፥ እንዳልኸው ልመናህን ተቀብዬሃለሁ፤
ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።