Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 8:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እም​ነ​ትሽ አዳ​ነ​ችሽ፤ በሰ​ላም ሂጂ” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ ፈውሶሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ኢየሱስም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ!” አላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:48
15 Referencias Cruzadas  

ኤል​ሳ​ዕም ንዕ​ማ​ንን፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው። ጥቂት መን​ገ​ድም ከእ​ርሱ ራቀ።


ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።


ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።


ኢየሱስም ለመቶ አለቃ “ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።


እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።


ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ! አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤” አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።


እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት።


እር​ሱ​ንም፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እይ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው።


ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”


ሴቲ​ቱም እን​ዳ​ል​ተ​ሰ​ወ​ረ​ላት ባየች ጊዜ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ሄዳ ሰገ​ደ​ች​ለት፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በምን ምክ​ን​ያት ወደ እርሱ እንደ ቀረ​በ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ እንደ ዳሰ​ሰች ወዲ​ያ​ውም እንደ ዳነች ተና​ገ​ረች።


እር​ሱም ጳው​ሎ​ስን ሲያ​ስ​ተ​ምር ሰማው፤ ጳው​ሎ​ስም ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፤ እም​ነት እን​ዳ​ለ​ውና እን​ደ​ሚ​ድ​ንም ተረዳ።


አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ለእ​ነ​ዚያ ደግሞ እንደ ተነ​ገረ ለእ​ኛም የም​ሥ​ራች ተሰ​ብ​ኮ​ል​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ሙት ቃል ከሰ​ሚ​ዎቹ ጋር በእ​ም​ነት ስላ​ል​ተ​ዋ​ሐደ አል​ጠ​ቀ​ማ​ቸ​ውም።


ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos