La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 24:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አለው፤ “ክፉ ሳደርግብህ፣ በጎ መልሰህልኛልና፣ አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲያበቃ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ሲል ጠየቀው፤ ሳኦል ጮኾም አለቀሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትን አለው፦ እኔ ክፉ በመለስሁልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 24:17
8 Referencias Cruzadas  

ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።


እጅግ ጐሰ​ቈ​ልሁ፥ ጐበ​ጥ​ሁም፥ ሁል​ጊ​ዜም በት​ካዜ እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤


ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን።


“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


ሳኦ​ልም የዳ​ዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ” አለው።


ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመ​ለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐ​ይ​ንህ ፊት ከብ​ራ​ለ​ችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላ​ደ​ር​ግ​ብ​ህም፤ እነሆ፥ ስን​ፍና እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወ​ቅሁ” አለ።