1 ሳሙኤል 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመጣችሁት እኔ የእብዶች አለቃ ነኝን? እንዲህ ያለውስ ወደ ቤቴ ይገባልን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ ዐጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ አጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ዘንድ እንዲያብድ ወደ እኔ ይህን ሰው ያመጣችሁት፥ እኔ እብድ አጥቼ ነውን? ይህ ሰው ወደ ቤቴ መግባት አለበትን?” አላቸው። |
ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ አመለጠ፤ ወደ ዔዶላም ዋሻም መጣ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደዚያ ወረዱ።