ያዕቆብም ተቈጣ፤ ላባንም ወቀሰው፤ ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “የበደልሁህ በደል ምንድን ነው? ኀጢአቴስ ምንድን ነው? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ?
1 ሳሙኤል 20:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፥ “ስለ ምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም፣ “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” ሲል አባቱን ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፦ ስለ ምን ይሞታል? ያደረገውስ ምንድር ነው? ብሎ መለሰለት። |
ያዕቆብም ተቈጣ፤ ላባንም ወቀሰው፤ ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “የበደልሁህ በደል ምንድን ነው? ኀጢአቴስ ምንድን ነው? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ?
ከፀሓይ በታች የተደረገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸው ሳሉ ሁከት በልባቸው አለ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ጲላጦስም ለሦስተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት አላገኘሁበትም፤ እንኪያስ ልግረፈውና ልተወው” አላቸው።
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካም ተናገረ እንዲህም አለው፥ “እርሱ አልበደለህምና፥ ሥራውም ለአንተ እጅግ መልካም ሆኖአልና ንጉሡ ባሪያውን ዳዊትን አይበድለው፤
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”
ዳዊትም ከአውቴዘራማ ሸሸ፤ ወደ ዮናታንም መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “ምን አደረግሁ? ምንስ በደልሁ? ነፍሴንም ይሻት ዘንድ በአባትህ ፊት ጥፋቴና ኀጢአቴ ምንድን ነው?”
አቤሜሌክም መልሶ ንጉሡን፥ “ከባሪያዎቹ ሁሉ የታመነ፥ ለንጉሥም አማች የሆነ፥ የትእዛዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤትህም የከበረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው?