ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተወደድህ ነበርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።
1 ሳሙኤል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ዳዊትን እንደ ነፍሱ ይወድድ ነበርና እንደ ገና ማለለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊት እንደ ገና እንዲምልለት አደረገ፤ ዳዊትን የሚወድደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊትን የሚወደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ አድርጎ ይወደው ስለ ነበር “በእርግጥ እንደምትወደኝ ለመግለጥ እንደገና ማልልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ዳዊትን እንደ ነፍሱ ይወድድ ነበርና እንደ ገና ማለለት። |
ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተወደድህ ነበርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።
የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፤ በምድር ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳኦል መንገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፤ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።