እርሱም ልዩ የሆነውን ግብፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብፃዊውም በእጁ ዛቢያው እንደ ድልድይ ዕንጨት የሆነ ጦር ነበረው፤ በናያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
1 ሳሙኤል 17:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፤ ገደለውም፤ ራሱንም ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዝዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሱም ሮጦ በመሄድ በላዩ ላይ ቆመ፤ የጎልያድንም ሰይፍ ከሰገባው በመምዘዝ ራሱን ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም የእነርሱ ዝነኛ ተዋጊ ጎልያድ መገደሉን ባዩ ጊዜ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ። |
እርሱም ልዩ የሆነውን ግብፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብፃዊውም በእጁ ዛቢያው እንደ ድልድይ ዕንጨት የሆነ ጦር ነበረው፤ በናያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያቡስቴ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት፥ በዓረባም መንገድ ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ።
የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ።
ልጆች በሥጋና በደም አንድ ናቸውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእነርሱም እንደ ወንድም ሆነላቸው፤ መልአከ ሞትን በሞቱ ይሽረው ዘንድ፥ ይኸውም ሰይጣን ነው።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ ፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው።
አገላብጠውም የጦር መሣሪያዎችን ገፈፉ፤ በዙሪያቸውም ላሉ ለጣዖታቱና ለሕዝቡ የምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ሁሉ ላኩ።