ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
1 ሳሙኤል 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊቱም ቆመ፤ እጅግም ወደደው፤ ለእርሱም ጋሻ ጃግሬው ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ወደ ሳኦል መጥቶ አገልግሎቱን ጀመረ፤ ሳኦልም እጅግ ወደደው፣ እርሱም የሳኦል ጋሻ ጃግሬ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ወደ ሳኦል መጥቶ አገልግሎቱን ጀመረ፤ ሳኦልም እጅግ ወደደው፥ እርሱም የሳኦል ጋሻ ጃግሬ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ወደ ሳኦል መጥቶ ሥራውን ጀመረ፤ ሳኦልም በጣም ስለ ወደደው የእርሱ መሣሪያ ያዥ ጋሻጃግሬ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ሳኦል መጣ፥ በፊቱም ቆመ፥ እጅግም ወደደው፥ ለእርሱም ጋሻ ጃግሬው ሆነ። |
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
ሚስቶችህ የተመሰገኑ ናቸው፤ በፊትህ ሁልጊዜ የሚቆሙ፥ ጥበብህን የሚሰሙ እነዚህ አገልጋዮችህም ምስጉኖች ናቸው።
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።
እርሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግሬውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፤ ጐልማሳውም ወጋው፤ አቤሜሌክም ሞተ።
ሳኦልም ዳዊትን ፍልስጥኤማዊውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአቤኔር፥ “አቤኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ አላውቅም” አለ።