ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
1 ሳሙኤል 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ በመንገድ እንደ ተዋጉ በእስራኤል ላይ ክፉ ያደረጉትን አማሌቃውያንን ዛሬ እበቀላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፣ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ። |
ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
ወንጀላቸውን አንድ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው እንደ አሰቡ ክፋታቸውን ሁሉ ዐሰብሁ፤ አሁንም ክፋታቸው ከብባቸዋለች፤ በደላቸውም በፊቴ አለች።