እርስዋም በደጅ ስትገባ አኪያ የእግርዋን ኮቴ ሰማ፤ እንዲህም አላት፥ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለምንስ ራስሽን ለወጥሽ? እኔም የሚያስጨንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተልኬአለሁ።
1 ሳሙኤል 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ” አለው፤ እርሱም፥ “ተናገር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታ እግዚአብሔር የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ! ትናንት ማታ ጌታ የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፥ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም “ተወው በቃ፤ እግዚአብሔር ትናንትና ማታ የገለጠልኝን እነግርሃለሁ” አለው። ሳኦልም “እሺ ንገረኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፥ እርሱም፦ ተናገር አለው። |
እርስዋም በደጅ ስትገባ አኪያ የእግርዋን ኮቴ ሰማ፤ እንዲህም አላት፥ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለምንስ ራስሽን ለወጥሽ? እኔም የሚያስጨንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተልኬአለሁ።
አሁንም ቁሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እፋረዳችኋለሁ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ያደረገውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ እነግራችኋለሁ።
ሳኦልም፦“ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ ከበጎችና ከላሞች መንጋዎች መልካም መልካሙን አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አመጣን፤ የቀሩትንም ፈጽሜ አጠፋሁ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።
እነርሱም በከተማዪቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ብላቴናው ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእግዚአብሔርን ቃል ስማ” አለው። ብላቴናውም አለፈ።