1 ሳሙኤል 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደኛዋ መንገድ በማኪማስ አንጻር በመስዕ በኩል የምትመጣ ናት፤ ሁለተኛዋም መንገድ በገባዖን አንጻር በአዜብ በኩል የምትመጣ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱ ዐለት በስተሰሜን በኩል በማክማስ አንጻር፣ ሌላው ደግሞ በስተ ደቡብ በኩል በጌባዕ አንጻር ይገኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድንጋዮቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተ ደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአለቶቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱም ሾጣጣ በማክማስ አንጻር በሰሜን በኩል፥ ሁለተኛውም በጊብዓ አንጻር በደቡብ በኩል የቆሙ ነበሩ። |
ሳሙኤልም፥ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” አለ። ሳኦልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በነገርኸኝ መሠረት በቀጠሮው ቀን እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማኪማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፤
ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።
ዮናታንም በኮረብታው የነበሩትን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፤ ሳኦልም፦ እስራኤል ይስሙ ብሎ በሀገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ።
ዮናታንም ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ሊሻገርበት በወደደው መተላለፊያ መካከል በወዲህ አንድ ሾጣጣ፥ በወዲህም አንድ ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ፤ የአንዱም ስም ባዚስ፥ የሁለተኛውም ስም ሴና ነበረ።
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው።