ራሔልም ለያዕቆብ ልጅ እንዳልወለደች በአየች ጊዜ በእኅቷ ላይ ቀናችባት፤ ያዕቆብንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአልሆነ እሞታለሁ” አለችው።
1 ሳሙኤል 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በልብዋ አዝና አለቀሰች፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናም በነፍሷ ተመርራ አብዝታ በማልቀስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከልቧ ኀዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ ጌታ ጸለየች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ከልብዋ ሐዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ እግዚአብሔር ጸለየች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፥ በእግዚአብሔርም ፊት ጸለየች፥ ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች። |
ራሔልም ለያዕቆብ ልጅ እንዳልወለደች በአየች ጊዜ በእኅቷ ላይ ቀናችባት፤ ያዕቆብንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአልሆነ እሞታለሁ” አለችው።
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ደግሞም ንጉሡና ብላቴኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።
ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እንዳለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በልባቸው መራሮችና ኀያላን መሆናቸውን አባትህንና ሰዎቹን ታውቃለህ፤ አባትህ አርበኛ ነው፤ ሕዝቡንም አያሰናብትም።
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
ዐይኖች ደከሙ፤ ወደ ሰማይም ወደ እግዚአብሔር ማየት አልቻልሁም። ጌታ ሆይ፦ ይቅር በለኝ፤ የሰውነቴንም መከራ አርቅልኝ።
እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች፥ በልጅነቷም እንደ ተጠላች ሴት የጠራሽ አይደለም፥ ይላል አምላክሽ።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም ሀገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ፤ አትዘኑለትም።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።
ሕዝቡም ወደ ቤቴል መጥተው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ጽኑዕ ልቅሶ አለቀሱ።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
በሴሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነሣች። በሴሎም በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።