ከሳሪራ ሀገር የሆነ የኤፍሬማዊው የናባጥና ሳሩሃ የተባለች የመበለት ልጅ ኢዮርብዓም የሰሎሞን አገልጋይ ነበረ።
1 ሳሙኤል 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ የኤያሬምኤል ልጅ፣ የኢሊዩ ልጅ፣ የቶሑ ልጅ፣ የናሲብ ልጅ፣ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራማ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ የሚኖር ትውልዱ ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ ሕልቃና ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ የኤሊሁ የልጅ ልጅ ሲሆን፥ ኤሊሁ ደግሞ የቶሑ ልጅ የጹፍ የልጅ ልጅ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራራማው በኤፍሬም አገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ስሙ ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ነበረ፥ እርሱም የኢያሬምኤል ልጅ የኢሊዮ ልጅ የቶሑ ልጅ የናሲብ ልጅ ነበረ። |
ከሳሪራ ሀገር የሆነ የኤፍሬማዊው የናባጥና ሳሩሃ የተባለች የመበለት ልጅ ኢዮርብዓም የሰሎሞን አገልጋይ ነበረ።
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ።
በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ።
እርስዋም በኤፍሬም ተራራ በቤቴልና በኢያማ መካከል “የዲቦራ ዘንባባ” ተብሎ በሚጠራው ዛፍ ሥር ተቀምጣ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር።
የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።
ማልደውም ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ ወደ ቤታቸውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም።
ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስምንት ልጆችም ነበሩት፤ እሴይም በሳኦል ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።
በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተዉት። እነርሱም ወደ አርማቴም ወደ ቤታቸው ገቡ፤ ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
ወደ ተራራማውም ወደ ኤፍሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲልካ ምድርም አለፉ፤ አላገኙአቸውምም፤ በፋስቂም ምድር አለፉ፤ በዚያም አልነበሩም፤ በኢያሚንም ምድር አለፉ፤ አላገኙአቸውምም።
ወደ መሴፋ ምድርም በደረሱ ጊዜ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፥ “አባቴ ስለ አህዮች ማሰብን ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፤ እንመለስ” አለው።