Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሩት 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰውዬው ስም ኤሊሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ናዖሚ፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ እነርሱም የቤተልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ፥ በዚያም ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሰውዬው ስም ኤቤሜሌክ፥ የሚስቱ ስም ናዖሚ፥ የሁለቱ ልጆች ስም ማሕሎንና ኬሌዎን ይባል ነበር፤ በትውልዱ ኤፍራታዊ ሆኖ በቤተልሔም ከተማ የሚኖር ነበር፤ እርሱም ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄዶ ኖረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar




ሩት 1:2
11 Referencias Cruzadas  

ራሔ​ልም ሞተች፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም በም​ት​ወ​ስድ መን​ገድ ተቀ​በ​ረች፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


በይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ከይ​ሁዳ ወገን የሆነ አንድ ጐል​ማሳ ነበረ፤ እር​ሱም ሌዋዊ ነበረ፤ በዚ​ያም ይቀ​መጥ ነበር።


በዚ​ያም ወራት ሞዓ​ባ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ገቡ፤ ምድ​ሪ​ቱም ሰማ​ንያ ዓመት ዐረ​ፈች። ናዖ​ድም እስ​ኪ​ሞት ድረስ ገዛ​ቸው።


የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ፣ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ።


መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ ሞቱ፣ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።


ለኑኃሚንም ባል የሚዛመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።


ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።


ዳዊ​ትም የዚያ የኤ​ፍ​ራ​ታ​ዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስም​ንት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ እሴ​ይም በሳ​ኦል ዘመን በዕ​ድሜ አር​ጅቶ ሸም​ግ​ሎም ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትም ፊት ለፊት ተሰ​ላ​ል​ፈው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos