Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም አንዲቱ ሐና፣ ሌላዪቱ ፍናና የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍናና ልጆች ሲኖሯት፣ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም አንዲቱ ሐና፥ ሁለተኛዪቱም ጵኒና ነበር። ጵኒና ልጆች ነበሯት፤ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሕልቃናም ሐናና ፍኒና ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍኒና ልጆች ነበሩአት፤ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሁለትም ሚስቶች ነበሩት የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፥ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፥ ለሐና ግን ልጅ አልነበራትም።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 1:2
13 Referencias Cruzadas  

ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች።


ላሜ​ሕም ለራሱ ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ስም ሴላ ነበር።


ላሜ​ሕም ለሚ​ስ​ቶቹ ለዓ​ዳና ለሴላ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የላ​ሜሕ ሚስ​ቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጡ፤ እኔ ጐል​ማ​ሳ​ውን ስለ መቍ​ሰሌ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ስለ መወ​ጋቴ ገድ​የ​ዋ​ለ​ሁና፤


እርሱም “ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።


ከአ​ሴር ወገን የም​ት​ሆን የፋ​ኑ​ኤል ልጅ ሐና የም​ት​ባል ነቢ​ይት ነበ​ረች፤ አር​ጅ​ታም ነበር፤ ከድ​ን​ግ​ል​ና​ዋም በኋላ ከባል ጋር ሰባት ዓመት ኖረች።


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር።


ለጌ​ዴ​ዎ​ንም ብዙ ሚስ​ቶች ነበ​ሩ​ትና ከአ​ብ​ራኩ የወጡ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos