1 ጴጥሮስ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመልካም ነገር ቀናኢ ብትሆኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ነገር ለማድረግ ብትተጉ ጒዳት የሚያደርስባችሁ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? |
ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መልካም ለሚሠራ የሚአስፈሩ አይደሉም፤ ሹሞችን እንዳትፈራ ብትፈልግ መልካም አድርግ፤ እነርሱ ደግሞ ያመሰግኑሃል፤
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።