1 ነገሥት 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞሬዎናውያንና ከኬጤዎናውያን፥ ከከናኔዎን፥ ከፌርዜዎናውያን፥ ከኤዌዎናውያን፥ ከኢያቡሴዎናውያንና ከጌርጌሴዎናውያን፥ የቀሩትን አሕዛብ ሁሉ፥ ከእነርሱም በኋላ በምድሪቱ የቀሩትን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ያልሆኑትን ከአሞራውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን የተረፉትን ሕዝቦች ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ሕዝብ ያልሆኑትን ከአሞራውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤው ያውንና ከኢያቡሳውያን ሕዝቦች ሁሉ የተረፉትን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሰሎሞን የጒልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ትውልዶች ነበሩ፤ እነዚህም ትውልዶች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞራውያንና ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከሒዋውያንና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን፥ |
ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፤ የሰረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም፥ በሊባኖስም፥ በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ።
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ።
መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።
በምሥራቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞሬዎናዊውም፥ ወደ ኬጤዎናዊውም፥ ወደ ፌርዜዎናዊውም፥ በተራራማውም ሀገር ወዳለው ወደ ኢያቡሴዎናዊው፥ በቆላማውና በመሴፋ ወዳለው ወደ ኤዌዎናዊዉም ላከ።
እነርሱም አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበዓልሄርሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዌዎናውያን፤
የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን፥ በኬጤዎናውያን፥ በአሞሬዎናውያን፥ በፌርዜዎናውያን፥ በኤዌዎናውያን፥ በኢያቡሴዎናውያንም መካከል ተቀመጡ።