Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በአጠቃላይ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በግዛቶቹ ሁሉ ለመሥራት የፈለጋቸውን ነገሮች፣ ዕቃ የሚከማችባቸውን ከተሞች፣ እንዲሁም ሠረገለኞችና ፈረሰኞች የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 9:19
9 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።


አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ከዚ​ህም በኋላ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት፥ የን​ጉ​ሡን ቤትና ሰሎ​ሞን ያደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠርቶ በፈ​ጸመ ጊዜ፥


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ያል​ነ​በ​ሩ​ትን ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከከ​ና​ኔ​ዎን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንና ከጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ የቀ​ሩ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ በም​ድ​ሪቱ የቀ​ሩ​ትን፥


ሰሎ​ሞ​ንም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሰበ​ሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረ​ገ​ሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎች ከተ​ሞ​ችም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው። ሕዝ​ቡም ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበሩ።


በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


ዐይ​ኖቼ ከፈ​ለ​ጉት ሁሉ አላ​ጣ​ሁም፥ ልቤ​ንም ከደ​ስታ ሁሉ አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም፤ ልቤ በድ​ካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበ​ርና፤ ከድ​ካ​ሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋን​ታዬ ሆነ።


በዐ​ይን ማየት በነ​ፍስ ከመ​ቅ​በ​ዝ​በዝ ይሻ​ላል፥ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos