ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ። ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።
1 ነገሥት 7:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥርም የናስ መቀመጫዎችን ሠራ፤ የአንዱም መቀመጫ ርዝመት አራት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ዐሥር ባለመንኰራኵር የዕቃ ማስቀመጫዎች ከመዳብ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ርዝመት አራት ክንድ፣ ወርድ አራት ክንድ፣ ቁመትም ሦስት ክንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑራም የእያንዳንዱ ርዝመት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ወርዱ አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር የሆነ ዐሥር ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑራም የእያንዳንዱ ርዝመት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ወርዱ አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር የሆነ ዐሥር ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዐሥርም የናስ መቀመጫዎች ሠራ፤ የአንዱም መቀመጫ ርዝመት አራት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ ነበረ። |
ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ። ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።
ዐሥሩንም የናስ መታጠቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታጠቢያ ሰን አርባ የባዶስ መስፈሪያ ያነሣ ነበር፤ እያንዳንዱም መታጠቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐሥሩም መቀመጫዎች ላይ በእያንዳንዱ አንድ አንድ መታጠቢያ ሰን ይቀመጥ ነበር።
ንጉሡ አካዝም የመቀመጫዎችን ክፈፍ ቈረጠ፤ ከእነርሱም የመታጠቢያውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬውንም ከበታቹ ከነበሩት ከናሱ በሬዎች አወረደው፤ በጠፍጣፋውም ድንጋይ ላይ አኖረው።
ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዓምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬዎች ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኵሬ መቀመጫዎቹንም ወሰደ፤ ለእነዚህም ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረውም።
ስላልወሰዳቸው ዓምዶች፥ ስለ ባሕሩም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦
ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የናስ ዐምዶች በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናሱን ኩሬ ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ የናስ ዕቃዎች ሁሉ ሚዛን አልነበራቸውም።