1 ነገሥት 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የታችኛውም ደርብ ወርዱ አምስት ክንድ፥ የመካከለኛውም ደርብ ወርዱ ስድስት ክንድ፥ የሦስተኛውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረገሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እንዳይገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ አረፍቶችን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ቤቱ ወርድ ዐምስት ክንድ፣ የመካከለኛው ፎቅ ስድስት ክንድ፣ የሦስተኛው ፎቅ ሰባት ክንድ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ዘልቆ እንዳይገባም፣ ከቤተ መቅደሱ ግንብ ውጭ ዙሪያውን እርከኖች አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታችኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የሁለተኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ ሁለት ሜትር ከሰባ ሳንቲ ሜትር፥ የመጨረሻው ፎቅ ክፍል ወርዱ ሦስት ሜትር ከዐሥር ሳንቲ ሜትር ነበር፤ የእያንዳንዱም ወለል ግንብ ከታች በኩል ካለው የወለል ግንብ የሳሳ ነበር፤ ሠረገሎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግድግዳ እንዳይገቡ ለማድረግ ከቤተ መቅደሱ ግድግዳ ውጪ ዐረፍቶችን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታችኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የሁለተኛው ፎቅ ክፍል ወርድ ሁለት ሜትር ከሰባ ሳንቲ ሜትር፥ የመጨረሻው ፎቅ ክፍል ወርድ ሦስት ሜትር ከዐሥር ሳንቲ ሜትር ነበር፤ የእያንዳንዱ ወለል ግንብ ከታች በኩል ካለው የወለል ግንብ የሳሳ ነበር፤ ሠረገሎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግድግዳ እንዳይገቡ ለማድረግ ከቤተ መቅደሱ ግድግዳ ውጪ ዐረፍቶችን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታችኛውም ደርብ ወርዱ አምስት ክንድ፥ የመካከለኛው ደርብ ወርዱ ስድስት ክንድ፥ የሦስተኛውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረገሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እንዳይገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ ዓረፍቶች አደረገ። |
ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ ሲሠሩትም መራጃና መጥረቢያ፥ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም።
ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፤ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ደገፋዎች ይሆኑ ዘንድ አረፍቶች ነበሩ፤ ከመቅደሱ ግንብ ጋር ግንአልተያያዙም ነበር።