Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጓዳ​ዎ​ቹም አንዱ ከአ​ንዱ በላይ በሦ​ስት ደርብ ነበሩ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳ​ዎች ነበሩ። በመ​ቅ​ደ​ሱም ግንብ ዙሪያ ደገ​ፋ​ዎች ይሆኑ ዘንድ አረ​ፍ​ቶች ነበሩ፤ ከመ​ቅ​ደሱ ግንብ ጋር ግን​አ​ል​ተ​ያ​ያ​ዙም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎች፣ ባለሦስት ደርብ ናቸው፤ በእያንዳንዱም ደርብ ላይ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ፤ በግንቡም ዙሪያ ግራና ቀኝ ያሉትን እነዚህን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ ሆኖም ተሸካሚዎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ ሆነው የተሠሩ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ላይ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በቤቱ ግንብ ውስጥ የተደገፉ ስላልነበሩ፥ ቤቱ በዙሪያው ላሉት ጓዳዎች ያለው ግንብ ውስጥ እንዲደገፉ ግንቡ ውስጥ ገቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነዚህም ክፍሎች አንዱን በአንዱ ላይ በመቀጠል ሦስት ፎቅ ሆነው ተሠርተው፥ እያንዳንዱ ፎቅ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩት፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ ያለው የቤተ መቅደሱ ውጫዊ ግንብ በታችኛው ካለው ፎቅና ግንብ ይልቅ የሳሳ ነበር፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በቤተ መቅደሱ ሕንጻ ላይ ሳያርፍ፥ ክፍሎቹ የተደገፉት በዚያው በዋናው ግንብ ስለ ነበር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ደገፋዎች ይሆኑ ዘንድ አረፍቶች ነበሩ፥ በመቅደሱም ግንብ ውስጥ ደገፉዎች አልነበሩም።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:6
6 Referencias Cruzadas  

በቤ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ቁመ​ታ​ቸው አም​ስት አም​ስት ክንድ የሆኑ ደር​ቦ​ችን ሠራ፤ ከቤ​ቱም ጋር በዝ​ግባ እን​ጨት አጋ​ጠ​ማ​ቸው።


ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ግንብ ስድ​ስት ክንድ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉ​ትን የጓ​ዳ​ዎ​ቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


በሦ​ስ​ትም ደርብ ተሠ​ር​ተው ነበ​ርና፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም እን​ዳ​ሉት አዕ​ማድ፥ አዕ​ማድ አል​ነ​በ​ሩ​ላ​ቸ​ው​ምና ስለ​ዚህ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኞ​ቹና ከታ​ች​ኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos