Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በቤ​ቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነ​በ​ሩት አረ​ፍ​ቶች ምክ​ን​ያት ላይ​ኞቹ ጓዳ​ዎች ከታ​ች​ኞቹ ጓዳ​ዎች ይበ​ልጡ ነበር፤ ከታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወደ ሦስ​ተ​ኛው የሚ​ወ​ጣ​በት ደረጃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያሉት ክፍሎች ስፋት በየደርቡ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ሕንጻ አሠራሩ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ፣ ወደ ላይ በተሄደ ቍጥር የክፍሎቹ ስፋት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመካከለኛው ደርብ በኩል አድርጎ ከታች ወደ ላይ የተዘረጋም ደረጃ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በቤቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነበሩት አረፍቶች ምክንያት ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር፤ ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የታችኛው ግድግዳ ከፎቁ ግድግዳ የወፈረ ነው፤ ሆኖም ከውጪ ሲመለከቱት ከላይ እስከ ታች ያለው ግድግዳ እኩል ውፍረት ያለው ይመስላል። ግድግዳዎቹ ከታች ወደላይ እየሳሱ ስለሚሄዱ ወደ ላይ በተወጣ ቊጥር ክፍሎቹ እየሰፉ ይሄዳሉ። መወጣጫዎቹም ከምድር ወደ ላይኛው ፎቅ የሚወጡት በመካከለኛው ፎቅ በኩል አድርገው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በቤቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነበሩት አረፍቶች ምክንያት ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር፥ ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:7
4 Referencias Cruzadas  

በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።


የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ጓዳ​ዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠ​ገብ ነበረ። ከዚ​ያም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው ደርብ፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ወደ ሦስ​ተ​ኛው ደርብ የሚ​ወ​ጡ​በት መውጫ ነበ​ረው።


እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”


ስለ​ዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን የነ​ገ​ሩን መጀ​መ​ሪያ ትተን ወደ ፍጻ​ሜው እን​ሂድ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ሌላ መሠ​ረት እን​ዳ​ትሹ ዕወቁ፤ ይኸ​ውም ከሞት ሥራ ለመ​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለማ​መን፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos