1 ነገሥት 6:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ሳንቃዎችን ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን፥ ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ የወይራ ዕንጨት ደጃፎች ሠራ፤ መቃኖቻቸውንና መድረኮቻቸውን ባለዐምስት ማእዘን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተከፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተከፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቅዱስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ደጆች ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። |
ሁለቱንም ሣንቃዎች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ፥ የፈነዳም አበባ ሥዕል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኪሩቤልንና የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጠ።
ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።