በዐሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዐቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባት ዓመትም ሠራው።
1 ነገሥት 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸመውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ዓይነት ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸመውም። |
በዐሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዐቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባት ዓመትም ሠራው።
እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የሰላሙን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ።
በድንኳኑና በመሠዊያውም ዙሪያ አደባባዩን ሠራ፤ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። እንዲሁም ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።