Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ቤቱ​ንም ሠርቶ ፈጸ​መው፤ የቤ​ቱ​ንም ጠፈር በዝ​ግባ ሳን​ቃ​ዎች አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ቤተ መቅደሱንም በዚሁ ሁኔታ ሠርቶ ጨረሰ፤ ለጣራው ተሸካሚ አደረገለት፤ በዝግባ ሳንቃም ከደነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚህ አኳኋን ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ለበደው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚህ አኳኋን ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖሱ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ለበደው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ቤቱንም ሠርቶ ፈጸመው፤ በዝግባው ሰረገሎችና ሳንቃዎች ከደነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:9
8 Referencias Cruzadas  

በቤ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ቁመ​ታ​ቸው አም​ስት አም​ስት ክንድ የሆኑ ደር​ቦ​ችን ሠራ፤ ከቤ​ቱም ጋር በዝ​ግባ እን​ጨት አጋ​ጠ​ማ​ቸው።


ሰሎ​ሞ​ንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸ​መ​ውም።


በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።


የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ጓዳ​ዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠ​ገብ ነበረ። ከዚ​ያም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው ደርብ፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ወደ ሦስ​ተ​ኛው ደርብ የሚ​ወ​ጡ​በት መውጫ ነበ​ረው።


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።


ሰሎ​ሞ​ንም በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የሰ​ላ​ሙን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሠ​ራው መሠ​ዊያ ላይ ያሳ​ርግ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ባለው መሠ​ዊያ ላይ ዕጣን ያሳ​ርግ ነበር፤ ቤቱ​ንም ጨረሰ።


በድ​ን​ኳ​ኑና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ አደ​ባ​ባ​ዩን ሠራ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ዘረጋ። እን​ዲ​ሁም ሙሴ ሥራ​ውን ፈጸመ።


የቤ​ታ​ችን ሰረ​ገላ የዝ​ግባ ዛፍ ነው፥ የጣ​ሪ​ያ​ች​ንም ማዋ​ቀ​ሪያ የጥድ ዛፍ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos