በዐዘቅተ መሐላ አጠገብም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቤሜሌክና ሚዜው አኮዞት፥ የሠራዊቱ አለቃ ፋኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።
1 ነገሥት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንደ ነገረው ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞንም መካከል ሰላም ነበረ፤ በመካከላቸውም ቃል ኪዳን አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በገባለት ተስፋ መሠረት ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከልም መልካም ግንኙነት ነበር፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንደ ነገረው ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞንም መካከል ሰላም ነበረ፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን ተጋቡ። |
በዐዘቅተ መሐላ አጠገብም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቤሜሌክና ሚዜው አኮዞት፥ የሠራዊቱ አለቃ ፋኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።
“በእኔና በአንተ መካከል በአባቴና በአባትህ መካከል ቃል ኪዳን ጸንቶአል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረከት ልኬልሃለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ ሄደህ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ” ብሎ ላከ።
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥሃለሁ። ካንተ በፊት ለነበሩ ነገሥታት ያልተሰጠውን፥ ከአንተም በኋላ ለሚነሡ የማይሰጠውን ብልፅግናን፥ ገንዘብንና ክብርን እሰጥሃለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የሰሎሞን ምርኮኞችን በኤዶምያስ ዘግተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኀጢአት አልመለስላቸውም።