Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 4:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን እጅግ ብዙ ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ የልብ ስፋ​ትን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን እንዲሁም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋትን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እግዚአብሔር ለሰሎሞን እጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሁም ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እግዚአብሔር ለሰሎሞን እጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሁም ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 4:29
19 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስን​ዴን አከ​ማቸ፤ መስ​ፈር እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ፤ ሊሰ​ፈር አል​ተ​ቻ​ለ​ምና።


እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።


እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ጥበ​ብን አበ​ዛሁ፤ ልቤ​ንም ለጥ​በ​ብና ለዕ​ው​ቀት ሰጠሁ፥” በማ​ለት ተና​ገ​ርሁ።


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


በዚያ ጊዜ አይ​ተሽ ትፈ​ሪ​ያ​ለሽ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብና የሀ​ገ​ሮች ብል​ጽ​ግና ወደ አንቺ ይመ​ለ​ሳ​ልና፥ ልብሽ ይደ​ነ​ግ​ጣል።


የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት መቍ​ጠር፥ የባ​ሕ​ር​ንም አሸዋ መስ​ፈር እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘርና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ኝን ሌዋ​ው​ያ​ንን አበ​ዛ​ለሁ።”


ሁሉም ለግፍ ሥራ ይመጣሉ፥ ፊታቸውንም እንደ ምሥራቅ ነፋስ ያቀናሉ፣ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባሉ።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ብዛ​ታ​ቸ​ውም እንደ አን​በጣ የሆነ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች ሁሉ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ሰፍ​ረው ነበር፤ የግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ቍጥር እን​ደ​ሌ​ለው በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos