Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አሞጽ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በምርኮ የሄዱትን ሕዝብ ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድማማቾችንም ቃል ኪዳን አላስታወሱምና ስለ ሦስት የጢሮስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 1:9
23 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ይዘ​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ምርኮ ማር​ከ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ይህም የሚ​ሆ​ነው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮ​ስ​ንና ሲዶ​ናን የቀ​ሩ​ት​ንም ረዳ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ታጠፋ ዘንድ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በከ​ፍ​ቶር ደሴት የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋ​ልና።


የጢ​ሮ​ስ​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የሲ​ዶ​ና​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ በባ​ሕር ማዶ ያሉ የደ​ሴት ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም፤


ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።


“ኮራዚ ወዮ​ልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮ​ልሽ! በእ​ና​ንተ የተ​ደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ተደ​ርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብ​ሰው አመ​ድም ነስ​ን​ሰው በተ​ቀ​መጡ ንስ​ሓም በገቡ ነበር።


ነገር ግን ጢሮ​ስና ሲዶና ከእ​ና​ንተ ይልቅ በፍ​ርድ ቀን ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛሉ።


ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።


በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


በፊቱ አን​ጻር በቆ​ምህ ቀን፥ አሕ​ዛብ ጭፍ​ራ​ውን በማ​ረ​ኩ​በት፥ እን​ግ​ዶ​ችም በበሩ በገ​ቡ​በት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዕጣ በተ​ጣ​ጣ​ሉ​በት ቀን አንተ ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ነበ​ርህ።


የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፣ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፣


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ኀይ​ል​ሽና ዋጋሽ፥ ንግ​ድ​ሽም፥ መር​ከ​በ​ኞ​ች​ሽም፥ መር​ከብ መሪ​ዎ​ች​ሽም፥ ሰባ​ራ​ሽን የሚ​ጠ​ግኑ ነጋ​ዴ​ዎ​ች​ሽም፥ በአ​ን​ቺም ዘንድ ያሉ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ሁሉ በው​ስ​ጥሽ ከአ​ሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወ​ደ​ቅ​ሽ​በት ቀን በባ​ሕር ውስጥ ይጠ​ፋሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios