አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
1 ነገሥት 20:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጾም አዋጅም ነገሩ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት በከፍተኛ ቦታ አስቀመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤን ሃዳድ ይህን መልእክት የሰማው ዐብረውት የነበሩት ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው በሚጠጡበት ጊዜ ነበር፤ ቤን ሃዳድ ሰዎቹን፣ “በሉ ለጦርነት ተዘጋጁ” አላቸው፤ ስለዚህ ከተማዪቱን ለመውጋት ተዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጾም አዋጅ ነገሩ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀመጡት። |
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
የእኩሌቶቹ ፈረሶች አለቃ ዘምሪም አሽከሮቹን ሁሉ ሰብስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በመጋቢው በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።
አክዓብም ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይዝራኤላዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወርሰው ተነሥቶ ወረደ።
እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፤ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ ጋሻዎቹንም በእነርሱ ላይ ያነሣል።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።